Sales & Field Agent
Kezyas Trading PLC
ስለ ስራው
ልክፈል App (LEKFEL App) በኢትዮጵያ የመጓጓዣ ክፍያን ዲጂታል ለማድረግ የሚሰራ የቴክኖሎጂ መፍትሔ ነው። በአዲስ አበባ የልክፈል App ተጠቃሚ አሽከርካሪዎችን ለማስመዝገብ እና ለማስጀመር የሚረዱ የሽያጭ እና የመስክ ወኪሎችን እየፈለግን ነው።
ኃላፊነቶች
- የታክሲ ማቆሚያዎችን እና የታክሲ መስመሮችን መጎብኘት
- ለአሽከርካሪዎች ስለ ልክፈል App ማስተዋወቅ
- አዲስ አሽከርካሪዎችን መፈለግ እና ማስመዝገብ
- የአሽከርካሪዎችን ምዝገባ በስማርት ስልክ ማጠናቀቅ
- የልክፈል Driver App እንዲጭኑ እና እንዲጠቀሙ መርዳት
- አሽከርካሪዎችን ስለ አፕሊኬሽኑ አጠቃቀም ማስረዳት
- የተመዘገቡ አሽከርካሪዎችን መከታተል እና አፕሊኬሽኑን መጠቀም እንዲጀምሩ ማገዝ
- የዕለት እና የሳምንት የምዝገባ ኢላማዎችን ማሳካት
መስፈርቶች
- 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች
- ጥሩ የመግባባት እና የማሳመን ችሎታ
- ከአሽከርካሪዎች ጋር በቀላሉ መግባባት የሚችል/ች
- በመስክ ላይ መስራት የሚችል/ች
- ተነሳሽነት ያለው እና ውጤት ላይ ያተኮረ/ች
- ስማርት ስልክ መጠቀም የሚችል/ች እና የራሱ/የራሷ ስማርት ስልክ ያለው/ላት
- የሽያጭ ወይም የመስክ ስራ ልምድ ቢኖር ይመረጣል (ግዴታ አይደለም)
ጥቅማ ጥቅሞች
- የወር መሠረታዊ ደመወዝ: 2,000 ብር
- በእያንዳንዱ አስመዝግቦ በአግባቡ በማስጀመር በሚያስችለው አሽከርካሪ ላይ ተጨማሪ ኮሚሽን