Driver
Darbar Business Group PLC
ስለ ስራው
Darbar Business Group PLC በሹፌርነት መደብ ላይ በሰሚት ወይም መገናኛ አካባቢ የሚኖር ሙሉ ጊዜ ሰራተኛ መቅጠር ይፈልጋል። የስራ ሰዓቱ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 ሲሆን ተቀጣሪው የድርጅት ሰራተኞችን፣ ንብረቶችን እና ተማሪዎችን በታማኝነት እና በኃላፊነት የማጓጓዝ ስራ ያከናውናል።
ኃላፊነቶች
- ሁሉንም የትራፊክ ሕጎች፣ የመንገድ ደህንነት ደንቦች እና የኩባንያ ፖሊሲዎችን ሁልጊዜ መከተል
- የድርጅቱን የሥራ መመሪያዎችና የሥራ ሰዓት አክብሮ መስራት
- የድርጅቱን ንብረት በኃላፊነትና በታማኝነት ለድርጅቱ ሥራ ብቻ በመጠቀም መስራት
- እንደተመደበው የኩባንያ ሠራተኞችን እና የኩባንያ ቁሳቁሶችን ማጓጓዝ
- የተመደበውን ተሽከርካሪ ንፅህና እና ደህንነት በተገቢ ሁኔታ መጠበቅ
- በየዕለቱ ለተሽከርካሪው ፍተሻዎችን ማድረግ እና ብልሽት፣ አደጋ ወይም ሌላ ችግር ሲያጋጥም ለሚመለከተው ኃላፊ ወዲያውኑ ማሳወቅ
- የተሽከርካሪውን ሰነዶች፣ ፈቃዶች እና ኢንሹራንስ ሁልጊዜ በትክክለኛ ቦታ ማስቀመጥ
- የነዳጅ አጠቃቀምን፣ የጉዞ ሪፖርትና ተያያዥ መዝገቦችን በትክክል በመመዝገብ በየሳምንቱ ሪፖርት ማድረግ
- ተግባራትን ሲያከናውኑ ሚስጥራዊነትን እና ሙያዊነትን መጠበቅ
መስፈርቶች
- ቢያንስ 10ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ ወይም ሰርተፍኬት ያለው
- 3 አመት እና ከዛ በላይ አግባብ ያለው የስራ ልምድ ያለው
- ህዝብ 1 የመንጃ ፈቃድ ያለው እና በቂ ተያዥ ማምጣት የሚችል
- በቤት መኪና (Corolla 2022 & Mercedes benz 2022 model) ተማሪን ት/ቤት ማድረስና መመለስ የሚችል እና ከዚህ ቀደም ልምድ ያለው
- ከትምህርት ቤት ማድረስ ሰዓት ውጪ የድርጅት ስራዎችን መስራት የሚችል
- ጾታ ወንድ እና እድሜ ከ35 አመት በላይ የሆናቸው
- የመኖሪያ አድራሻ ሰሚት ወይም መገናኛ አካባቢ የሚኖር
- ጥሩ የመግባቢያ እና የግለሰባዊ ግንኙነት ክህሎት ያለው
- መሰረታዊ የተሽከርካሪ ጥገና እውቀት ያለው
- አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ተለዋዋጭ የስራ ሰዓቶችን መሥራት የሚችል