P
Central Operations and payment lead/Dispatcher
Private Client
Job Type: Hybrid - Full Time
Education: Bachelor’s Degree
Experience: Intermediate
Skills: Customer Relationship Management, Customer Value & Profitability, Customer Relations, Customer Support & Success, Customer service skills, Customer Service
Central Operations & Payment Lead / Dispatcher
የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ – Central Office / Remote Console
የሥራ አይነት፦ ሙሉ ጊዜ
ክፍያ፦ የወር ደመወዝ + የአፈጻጸም ቦነስ
ስለ ሥራው
Dispatcher የዴሊቨሪ ሥራውን ከመሀል የሚቆጣጠር ሰው ነው። የደንበኞችን ትዕዛዝ ይከታተላል፣ ለDelivery ሹፌሮች ትዕዛዝ ይመድባል፣ የሬስቶራንት ክፍያዎችን ያስተናግዳል እና በDelivery ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮችን ይፈታል።
ዋና የሥራ ኃላፊነቶች
- አዲስ ትዕዛዞችን በCentral System ላይ መከታተል እና ለተገቢው Delivery ሹፌር መመደብ።
- የደንበኛ ክፍያዎችን በTelebirr/CBE ማረጋገጥ።
- ሹፌሩ ከሬስቶራንት የላከውን ደረሰኝ፣ QR ኮድ ወይም የአካውንት መረጃ በመመልከት የሬስቶራንቱን ክፍያ በፍጥነት መፈጸም።
- ሹፌሮችን ከPickup እስከ Delivery መከታተል።
- የትራፊክ፣ የመኪና ችግር፣ የሬስቶራንት መዘግየት ወይም ሌላ ችግር ሲኖር ፈጣን መፍትሔ መስጠት።
- ደንበኞችን በስልክ ወይም በመልዕክት ማገዝ።
- የምግብ እጥረት ወይም ሌላ የOrder ለውጥ ካለ ከደንበኛው ጋር ማስተባበር።
- የCOD ገንዘብን ከሹፌሮች ጋር በየቀኑ ማስማማት።
- የሬስቶራንት ክፍያዎች፣ የDelivery ክፍያዎች እና የተሰበሰበ COD ገንዘብ በትክክል መመዝገብ።
- የቀኑን የገንዘብ እና Operations ሪፖርት ማዘጋጀት።
- በRush Hour ጊዜ ብዙ ትዕዛዞችን በአንድ ጊዜ በትክክል ማስተናገድ።
የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- Diploma ወይም Bachelor’s Degree በBusiness Administration፣ Accounting፣ Logistics፣ IT ወይም ተዛማጅ ዘርፍ።
- በDispatch፣ Customer Service፣ Logistics ወይም Digital Payment ሥራ ልምድ ቢኖር ይመረጣል።
- Telebirr፣ CBE Mobile/USSD እና ሌሎች Digital Payment አገልግሎቶችን በቀላሉ መጠቀም የሚችል።
- የገንዘብ መጠን፣ የአካውንት ቁጥር እና Transaction መረጃ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርግ።
- በጫና ውስጥ በፍጥነት መሥራት እና ውሳኔ መስጠት የሚችል።
- ጥሩ የCommunication እና Customer Service ችሎታ።
- አማርኛ እና እንግሊዝኛ በጥሩ ሁኔታ መናገርና መጻፍ።
- Afaan Oromo ማወቅ ተጨማሪ ጥቅም ነው።
Apply ለማድረግ cv እና cover letter ያስፈልጋል::