Delivery Courier
Private Client
ስለ ሥራው
የምግብ ትዕዛዞችን ከተባባሪ ሬስቶራንቶች በመቀበል በደህናና በፍጥነት ለደንበኞች ማድረስ። ከCentral Operations/Dispatcher ቡድን ጋር በቅርበት በመስራት ትዕዛዙ ትክክል መሆኑን፣ ክፍያዎችን እና የዴሊቨሪ ሂደቱን ማረጋገጥ።
ኃላፊነቶች
- በተሰጠው ጊዜ ሬስቶራንት በመድረስ የደንበኛውን ትዕዛዝ ከተዘረዘረው ዝርዝር ጋር ማረጋገጥ
- የምግቡ ፓኬጅ በደንብ መዘጋቱን እና በዴሊቨሪ ቦርሳ ውስጥ በደህና መቀመጡን ማረጋገጥ
- የሬስቶራንቱን ደረሰኝ እና የክፍያ መረጃ ለOperations ቡድን መላክ
- ትዕዛዙን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለደንበኛው ማድረስ
- ለCash on Delivery (COD) ትዕዛዞች ከደንበኛው ትክክለኛውን ክፍያ መቀበል እና ካስፈለገ ትክክለኛ ተመላሽ መስጠት
- ስልክ፣ GPS እና Mobile Data በሥራ ሰዓት ንቁ ማድረግ
- የምግብ እጥረት፣ የሬስቶራንት መዘግየት፣ ወይም ደንበኛን ማግኘት ካልተቻለ ወዲያውኑ Dispatcher/Operations ቡድንን ማሳወቅ
- በየShift መጨረሻ የተቀበሉትን ገንዘብ እና የተጠናቀቁ ዴሊቨሪዎችን ከOperations ቡድን ጋር ማስማማት
መስፈርቶች
- ትክክለኛ የኢትዮጵያ የመንጃ ፈቃድ፣ እና በጥሩ ሁኔታ የሚሰራ ሞተር ሳይክል፣ ስኩተር ወይም ቀላል መኪና (ለተወሰኑ አካባቢዎች የእግረኛ እድልም ይኖራል)
- የሚሰራ ስማርትፎን፣ ጥሩ ካሜራ እና Mobile Data
- በራስ ስም የተመዘገበ Telebirr እና CBE አካውንት
- የአዲስ አበባን አካባቢዎች፣ ዋና መንገዶች እና የህንፃ/ማርከሮች አድራሻ አጠቃቀም በደንብ ማወቅ
- ታማኝ፣ በሰዓት የሚገኝ እና ለደንበኞች ጥሩ አገልግሎት የሚሰጥ መሆን
- ንፅህናን እና ሙያዊ አቀራረብን መጠበቅ
ጥቅማጥቅሞች
- የቀን/ሳምንት መሠረታዊ ክፍያ + በእያንዳንዱ ዴሊቨሪ ኮሚሽን