የተለያዩ ክፍት የስራ መደቦች
ካራቫን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስለ ስራው
ካራቫን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (Karavan Coffee) በተለያዩ ክፍት የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። የስራ ቦታዎች እንደ መደቡ አይነት መገናኛ፣ ቦሌ ብራስ፣ ቱሉዲምቱ፣ አየርጤና፣ 6 ኪሎ እና ቃሊቲ ሲሆኑ፣ ደመወዙ በስምምነት ነው።
መስፈርቶች
- ሱፐርቫይዘር (ብዛት 4) - በሆቴል አስተዳደርና በሆቴል ቱሪዝም የተመረቀ/ች፣ የስራ ልምድ 1 አመት እና ከዚያ በላይ፣ የስራ ሰዓት ግማሽ ቀን (12:45 – 9:00 ወይም 8:00 – 2:45)
- አስተናጋጅ (ብዛት 15) - በሆቴል መስተንግዶ የተመረቀ/ች፣ የስራ ልምድ 1 አመት እና ከዚያ በላይ፣ የስራ ሰዓት ግማሽ ቀን (12:45 – 9:00 ወይም 8:00 – 2:45)
- ካሸር (ብዛት 6) - ጾታ ሴት፣ 12ኛ ክፍል እና ከዚያ በላይ፣ በCNET ላይ 6 ወር የስራ ልምድ ያላት፣ የስራ ሰዓት (12:45 – 9:00 ወይም 8:00 – 2:45)
- ምግብ እና መጠጥ ቁጥጥር (ብዛት 5) - ጾታ ሴት፣ ዲፕሎማ እና ከዚያ በላይ፣ የስራ ልምድ 2 አመት እና ከዚያ በላይ፣ የስራ ሰዓት (12:45 – 9:00 ወይም 8:00 – 2:45)
- ስቶርኪፐር (ብዛት 3) - ዲፕሎማ እና ከዚያ በላይ፣ የስራ ልምድ 2 አመት እና ከዚያ በላይ፣ የስራ ሰዓት (12:45 – 9:00 ወይም 8:00 – 2:45)
እንዴት ማመልከት ይቻላል
በአካል ለመመዝገብ መገናኛ ቤቴልሔም ፕላዛ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 725 በአካል በመምጣት ማመልከት ይቻላል። ወይም በቴሌግራም @KARAVANCOFFEEHR ሙሉ ስም፣ ሰነዶች (ዶክመንት)፣ ስልክ ቁጥር እና ለየትኛው ብራንች ማመልከት እንደሚፈልጉ በመግለጽ ማመልከት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-90-38-48-12 መደወል ይቻላል።