የጥበቃ ሠራተኛ እና ሴት ፈታሽ
ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር
ስለ ሥራው
ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር ክፍት በሆነው የጥበቃ ሠራተኛ እና ሴት ፈታሽ የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
መስፈርቶች
- ትምህርት፡ 8ኛ ክፍል እና ከዚያ በላይ
- የሚፈለግ የሰው ኃይል፡ 12 የጥበቃ ሠራተኛ እና 2 ሴት ፈታሽ (በጠቅላላ 14)
- በጦር ሠራዊት/ወታደራዊ ሥልጠናና ልምድ ያለው (በክብር የተሸኘ)
- ዕድሜ ከ 30 ዓመት በላይ
- በንግድ ማዕከል፣ በኮሜርሻል ሕንፃ ወይም በተመሳሳይ የጥበቃ ሥራ ላይ ልምድ ያለው
- በፈረቃ ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ
- ተያዥ ማቅረብ የሚችል
- አካላዊ ብቃትና ንቁ የሆነ፣ ጥሩ የመግባባት ችሎታ ያለው
- የድርጅቱን የጥበቃና የደህንነት መመሪያዎችን ማክበር የሚችል
- የወንጀል መዝገብ የሌለው
ጥቅማ ጥቅሞች
- ደመወዝ በድርጅቱ ስኬል መሠረት
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አስፈላጊውን የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ዶክመንቶች በማሟላት ማስታወቂያው ከወጣበት (14/01/2019 ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ ከኩርቱ ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው አሜሪካን ጊቢ ህንፃ 4ኛ ፎቅ በአካል ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
የሥራ ቦታ፡ አዲስ አበባ (አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1፣ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ ከኩርቱ ህንፃ ፊት ለፊት፣ አሜሪካን ጊቢ ህንፃ)
ለበለጠ መረጃ፡ 0900333414 | 0909931111 | 0911696176