ሹፌር II
Minaye PLC
How to Apply
ስለ ሥራው
ሚናዬ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (Minaye PLC) በሹፌር II የሥራ መደብ ላይ 2 ክፍት የሥራ ቦታዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች በአግባቡ እና በጥንቃቄ መንዳት
- ተሽከርካሪዎችን በየቀኑ ስራ ከመጀመሩ በፊት የቅድመ-ፍተሻ (pre-trip inspection) ማድረግ
- የተሽከርካሪ ዘይት፣ የውሃ እና የጎማ ሁኔታን መከታተል
- ሰራተኞችን፣ እቃዎችን እና ሰነዶችን በደህንነት ወደ መድረሻቸው ማድረስ
- የተሽከርካሪ ሰነዶች (ሊሰንስ፣ ኢንሹራንስ፣ ቴክኒካል ፍተሻ) በጊዜው መከታተል
- የመንገድ ትራፊክ ህጎችን ሙሉ በሙሉ ማክበር
- የተሽከርካሪ ብልሽት ሲያጋጥም ወዲያውኑ ለኃላፊው ማሳወቅ
- ሌሎች በኃላፊው የሚሰጡ ተግባራትን ማከናወን
መስፈርቶች
- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ
- 2 ዓመት አግባብ ያለው የሥራ ልምድ
- ጥሩ የመንገድ እውቀት
- ጥሩ የስነ-ምግባር እና የተግባቦት ችሎታ
- በቡድን መስራት የሚችል
- ታማኝ እና ኃላፊነት የሚሰማው
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አመልካቾች የመንጃ ፍቃዳቸውን እና የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በኢሜል አድራሻችን talentaquisitionminaye@gmail.com ወይም ጦርሃይሎች በሚገኘው ቢሮአችን በአካል በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።