ጸሐፊ እና እንግዳ ተቀባይ (Secretary & Receptionist)
Private Client
Job Type: Onsite - Full Time
Education: Bachelor’s Degree
Experience: Senior
Vacancies: 1
Skills: Basic Writing
ዋልታ ቴክኖሎጂስ በድርጅቱ የቢሮ አስተዳደርና የእንግዳ አቀባበል ሥራዎች ላይ የምትሰማራ፣ ብቃትና የሥራ ልምድ ያላት ሴት ሠራተኛ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል።
1. የትምህርትና የሥራ ልምድ መስፈርቶች
በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሴክሬታሪያል ሳይንስ፣ በማኔጅመንት ወይም ተዛማጅ የትምህርት ዘርፍ ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ ያላት።
በተመሳሳይ የሥራ መስክ ቢያንስ 2 ዓመት የሥራ ልምድ ያላት።
በአማርኛና በእንግሊዝኛ ጥሩ የመጻፍና የመናገር ችሎታ ያላት።
የኮምፒውተር አጠቃቀም ብቃት ያላት (Microsoft Word, Excel, Outlook እና Email)።
2. ዋና ዋና የሥራ ኃላፊነቶች
የድርጅቱን እንግዶችና ደንበኞች በሥነ-ሥርዓትና በሙያዊነት መቀበልና ማስተናገድ።
የድርጅቱን የውስጥና የውጭ ደብዳቤዎች በትክክል ማዘጋጀት፣ መጻፍና መመዝገብ።
የመጡና የወጡ ደብዳቤዎችን በተደራጀ መንገድ መመዝገብና ማስቀመጥ።
የድርጅቱን ሰነዶችና ፋይሎች በሥርዓት ማደራጀትና መጠበቅ።
የዋጋ ዝርዝርና ፕሮፎርማ (Proforma Invoice) ማዘጋጀት።
የዕለት ገቢና ወጪ መዝገቦችን መያዝና በተገቢው ለሚመለከተው አካል ማቅረብ።
የሚመጡ እንግዶችን ስም፣ የመጡበትን ቀንና ሰዓት፣ የጉብኝታቸውን ምክንያትና የሚያገኙትን ሰው መመዝገብ።
የስልክ ጥሪዎችንና የኢሜይል መልዕክቶችን መቀበልና በአግባቡ ማስተላለፍ።
የቢሮ አስተዳደርና የጽሕፈት ሥራዎችን ማከናወን።
የቢሮ እቃዎችንና የጽሕፈት መሣሪያዎችን ፍላጎት መከታተልና መመዝገብ።
ከተለያዩ የድርጅቱ ክፍሎች ጋር በቅርበት በመሥራት የቢሮ ሥራዎች በሥርዓት እንዲከናወኑ ማስተባበር።
3. የግል ብቃትና የሥራ ባህሪ
ጠንካራ የመግባባትና የግንኙነት ችሎታ ያላት።
ተነሳሽነት (Proactiveness) እና የሥራ ፍላጎት ያላት።
ሥራዎችን በፍጥነት፣ በትክክልና በጥራት የማከናወን ችሎታ ያላት።
ጊዜን በአግባቡ የምትጠቀምና ብዙ ሥራዎችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ ችሎታ ያላት።
ምስጢር የመጠበቅና የሥራ ስነ-ምግባር ያላት።
በቡድን የመሥራትና ችግሮችን በተገቢው መንገድ የመፍታት ችሎታ ያላት።
ትእዛዝ እስኪሰጣት የማትጠብቅ፣ የሥራ ፍላጎትን በራሷ የምትለይና የምትፈጽም።
4. የሥራ ቦታና የቅጥር ሁኔታ
የሥራ ቦታ፦ ዋልታ ቴክኖሎጂስ፣ ደምበል አደባባይ / ኦሎምፒያ ሄይት ህንጻ፣ 11ኛ ፎቅ።
የሥራ ሁኔታ፦ በቋሚነት
የተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ፦ 15,000 ብር
5. የሥራ ሰዓት
ከሰኞ እስከ አርብ፦ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:00
ቅዳሜ፦ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30
6. ማመልከቻ
ለማመልከት የተሟላ CV፣ የትምህርት ማስረጃዎችና የሥራ ልምድ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማመልከቻዎን ያቅርቡ።
ማሳሰቢያ፦ የሥራ ልምድ፣ የደብዳቤ አጻጻፍ፣ የሰነድ አያያዝና የኮምፒውተር ብቃት በተግባር ይፈተናሉ።