Assistant Manager
Seri Skill Center Trading PLC
ስለ ሥራው
SERI Skill Center Trading PLC በአመራር፣ በማስተባበር እና በፕሮጀክት አስተዳደር ብቃት ያላትን ሴት ተወዳዳሪ በAssistant Manager የሥራ መደብ መቅጠር ይፈልጋል።
የሥራ ኃላፊነቶች
- የድርጅቱን ዕለታዊ ሥራዎች ማስተባበርና መከታተል
- የSERI ፕሮጀክቶችን ከእቅድ እስከ ትግበራ መምራት
- ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች ጋር በመስራት የጋራ ግቦችን ማሳካት
- የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም መከታተልና ሪፖርት ማቅረብ
- የስብሰባዎችን፣ የዝግጅቶችንና የልዩ ፕሮጀክቶችን ማስተባበር
- የሥራ እንቅፋቶችን መለየትና ተግባራዊ መፍትሔዎችን ማቅረብ
- የድርጅቱን ጥራት፣ ቅልጥፍናና የሥራ ባህል ማሻሻል
መስፈርቶች
- በManagement, Business Administration, Project Management ወይም ተዛማጅ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's Degree)
- ቢያንስ 2 ዓመት በሥራ አስተዳደር፣ በፕሮጀክት ማስተባበር ወይም በቡድን አመራር የሥራ ልምድ
- የፕሮጀክት እቅድ ማውጣት፣ ማስፈጸምና ውጤት መገምገም የምትችል
- በሪፖርት ዝግጅትና በሥራ ክትትል ጥሩ ብቃት ያላት
- በComputer Applications (Word, Excel, PowerPoint) ጥሩ ክህሎት ያላት
እንዴት ማመልከት ይቻላል
ፍላጎትና ብቃቱ ያላቸው እጩዎች የሚከተሉትን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፦
- Updated CV
- የትምህርት ማስረጃ
- የሥራ ልምድ ማስረጃ