አሽከርካሪ እና ጉዳይ አስፈጻሚ
Delta Rabbit Electron
ስለ ስራው
አሽከርካሪና ጉዳይ አስፈጻሚው ለድርጅቱ ሰራተኞች፣ እንግዶች እና እቃዎች አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት የመስጠት እንዲሁም የድርጅቱን የፊልድ ተግባራት እና የመንግስት ቢሮዎች ጉዳዮችን የማስፈጸም ሀላፊነት አለበት።
ሀላፊነቶች
- ለድርጅቱ ሰራተኞች፣ እንግዶች እና እቃዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሰአቱን የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት
- የተመደበውን ተሽከርካሪ ንጽህና መጠበቅ እና የዘይት፣ የውሃ፣ የጎማና የባታሪ እለታዊ ፍተሻ ማድረግ
- የትራፊክ ህጎችን ማክበር እና የእለታዊ ጉዞ ማስታወሻ ደብተር በጥንቃቄ መያዝ
- የድርጅቱን የውጭ ስራዎች፣ የሰነድ ልውውጦችን እና የመንግስት ቢሮ ጉዳዮችን መከታተልና ማስፈጸም
መስፈርቶች
- የዲፕሎማ ትምህርት ደረጃ
- በታወቀ ድርጅት ወይም ግብረ-ሰናይ ድርጅት ውስጥ አነስተኛ የ2 ዓመት የአሽከርካሪነት ስራ ልምድ
- ህጋዊ የህዝብ / የንግድ ማሽከርከር ፍቃድ (3ኛ ደረጃ / ህዝብ 1 / ደረቅ 1 ወይም ተመሳሳይ)
- በቂ ዋስትና ማቅረብ የሚችል
- ስለ አዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች እና መሰረታዊ የተሽከርካሪ ቴክኒክ በቂ እውቀት ያለው
- በጥሩ ደረጃ አማርኛ የሚናገርና የሚጽፍ፣ መሰረታዊ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያለው
- ታማኝነት፣ ሰዓት ማክበር፣ ሚስጥር ጠባቂነት እና ችግር የመፍታት ችሎታ