የፊልድ ላይ ሽያጭ ወኪል (Scout - Field Sales Agent)
Trego X Trading PLC
ስለ ሥራው
ትሬጎ ኤክስ ትሬዲንግ ከያንጎ (Yango) ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ከተማ ለሚያከናውነው የአሽከርካሪዎች እና ተጠቃሚዎች ምልመላ ስራ ቀልጣፋ እና ታታሪ የፊልድ ሴልስ ወኪሎችን (ስካውቶችን) ይፈልጋል። ይህ ሥራ ጠንክሮ በመሥራት በሥራ ውጤቱ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ለሚፈልጉ ግለሰቦች የተዘጋጀ ዕድል ነው።
ኃላፊነቶች
- በቢሾፍቱ ከተማ ዋና ዋና ቦታዎች በመንቀሳቀስ አዳዲስ አሽከርካሪዎችን እና ተጠቃሚዎችን መለየትና መመዝገብ
- የያንጎ መድረክ ጥቅሞች፣ የደህንነት ጥበቃዎች እና አጓጊ የገቢ ዕድሎች ለአሽከርካሪዎች እና ለደንበኞች በግልጽ ማስረዳት
- አሽከርካሪዎች አፑን ተጠቅመው እንዲመዝገቡና በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡ አስፈላጊውን ቴክኒካዊ ድጋፍ ማድረግ
- የተቋቋሙትን ዕለታዊ እና ሳምንታዊ የምዝገባና የሥራ ግቦች በብቃት ማሳካት
- የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎችን እና ውጤቶችን ለአስተባባሪዎች ሪፖርት ማድረግ
መስፈርቶች
- በጣም ጥሩ የሆነ የንግግር፣ የመግባባት እና የማሳመን ችሎታ ያለው/ላት
- በመስክ ላይ በንቃት ተንቀሳቅሶ ለመሥራት እና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመገናኘት ፍላጎትና ዝግጁነት ያለው/ላት
- መሠረታዊ የስማርት ስልክ እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ብቃት
- ለሥራው ትጋት ያለው፣ ኃላፊነት የሚሰማው እና በዕቅድና በውጤት (Target) መሥራት የሚችል/ቺ
- ቀደም ሲል በሽያጭ፣ በማርኬቲንግ ወይም በመስክ ማስተዋወቅ ሥራ ላይ ልምድ ያለው/ላት ቢሆን ይመረጣል
- የገጽታ እና የመንገድ ላይ ሽያጭ (Field Sales) ክህሎት፣ ደንበኞችን የመሳብ፣ ፈጣን ችግር ፈቺነት እና የጊዜ አጠቃቀም ችሎታ
ጥቅማጥቅሞች
- መሰረታዊ ደሞዝ 10,000 ብር + ማራኪ ኮሚሽን (በሥራዎ ልክ የሚያድግ ገቢ)
- ማራኪ የሥራ አካባቢ እና ከቡድን ጋር በቅንጅት የመሥራት ዕድል