የሂሳብ ክፍል ኃላፊ
ሁካኬብ ትሬዲንግ
ስለ ሥራው
ሁካኬብ ትሬዲንግ በፋይናንስና በአካውንቲንግ ዘርፍ የተካነ የሂሳብ ክፍል ኃላፊ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ተቀጣሪው የድርጅቱን የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች፣ የኦዲት ሰነዶችና የሂሳብ መዝገቦችን በኃላፊነት የሚያስተዳድር ይሆናል።
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
- የሁካኬብ ትሬዲንግ ገቢ፣ ወጪ፣ ንብረት፣ ዕዳና የባንክ ሂሳብ ለየብቻ መመዝገብና መቆጣጠር
- የባንክ ሂሳብ ማመሳሰል፣ የደንበኞችና የአቅራቢዎች ሂሳብ ክትትል ማከናወን
- ወርኃዊ የገቢና ወጪ፣ የገንዘብ ፍሰትና የቀሪ ሂሳብ ሪፖርቶችን ለእያንዳንዱ ድርጅት ማዘጋጀት
- የንግድ ቦታ ኪራይና የሽያጭ ክፍያዎችን ከውሎችና ከባንክ ማስረጃዎች ጋር ማመሳሰል እና የቀሪ ክፍያዎችን ሪፖርት ማቅረብ
- የሁካኬብን የማሽን ኪራይ፣ የግንባታ ውልና የማያቋርጥ ሥራ ገቢና ወጪ በሥራ ዘርፍ መከታተል
- የደመወዝ፣ የታክስና ሌሎች መደበኛ የሂሳብ ማስገቢያ ሰነዶችን በወቅቱ ማዘጋጀትና ማረጋገጥ
- ለኦዲት፣ ለባንክና ለዕመራር የሚፈለጉ የፋይናንስ ሰነዶችና ሪፖርቶችን በሥርዓት ማደራጀት
- ከአሁኑ የሂሳብ ሠራተኛ ጋር የሥራ ክፍፍል በማድረግ የመዝገቦችንና የማስረጃዎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ
መስፈርቶች
- በአካውንቲንግ፣ በፋይናንስ ወይም በተዛማጅ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ
- ከ 5 እስከ 7 ዓመት አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ
- የመኖሪያ አድራሻ ለሀይሌ ጋርመንት ቅርብ የሆነ
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አመልካቾች ሲቪያቸውን፣ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎቻቸውን በመላክ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ አመልክት/ቺ የሚለውን ይጫኑ፡፡
የማመልከቻ መጨረሻ ቀን፡ November 18, 2026