ስቶር ኪፐር
ሁካኤብ ትሬዲንግ እና ማሳለጫ ሪል ስቴት
ስለ ሥራው
ድርጅቱ በሁካኤብ ትሬዲንግ እና በማሳለጫ ሪል ስቴት የዕቃ መዝገብ አያያዝ እና አስተዳደር ሥራዎችን በኃላፊነት የሚያከናውኑ ሴት ስቶር ኪፐር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- ወደ ስቶር የሚገቡ ዕቃዎችን ከግዢ ትዕዛዝ፣ ደረሰኝና ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማነፃፀር በመጠን፣ በዓይነትና በጥራት መረከብ
- የዕቃ መረከቢያ ሰነድ ማዘጋጀት፣ የገባውን ዕቃ መመዝገብ እና በደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማስቀመጥ
- የሁካኤብ ትሬዲንግንና የማሳለጫ ሪል ስቴትን የዕቃ መዝገብ ለየብቻ መያዝ እና በተፈቀደ ሰነድ መሠረት ዕቃ ማሰራጨት
- የገባ፣ የወጣና የቀረ ዕቃ መረጃን በየቀኑ በኮምፒውተር ማዘመን እንዲሁም የተበላሹ ወይም የጠፉ ዕቃዎችን ሪፖርት ማድረግ
- የዕቃ መጠን ሲያንስ የግዢ ፍላጎትን ቀድሞ ማሳወቅ እና ሳምንታዊና ወርሃዊ የቆጠራ ሪፖርቶችን ማቅረብ
መስፈርቶች
- በአቅርቦትና ግዢ አስተዳደር፣ በሎጂስቲክስ፣ በአካውንቲንግ፣ በቢዝነስ አስተዳደር ወይም በተመሳሳይ መስክ ዲፕሎማ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ
- ከ 1 እስከ 3 ዓመት አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ
- ለሴት አመልካቾች ብቻ
- የመኖሪያ አድራሻ ለሀይሌ ጋርመንት ቅርብ የሆነ
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አመልክት/ቺ የሚለውን ይጫኑ።
ማስታወሻ፡ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች የተዘመነ CV፣ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ፣ የቀድሞ አሠሪዎች ማጣቀሻና የመገኛ ስልክ፣ የደመወዝ ጥበቃና ሥራ መጀመር የሚችሉበት ቀን በመጥቀስ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡