የመዝገብ ቤት ባለሙያ (Registry Officer)
Abol Technologies PLC
ስለ ሥራው
Abol Technologies PLC በሙሉ ጊዜ (Onsite) የሚሰራ ጀማሪ የመዝገብ ቤት ባለሙያ (Registry Officer) ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- ሰነዶችን በዓይነትና በቀን መለየት እንዲሁም በአግባቡ ፋይል ማድረግ
- የተቀመጡ ሰነዶችን በደህና መጠበቅ እና የጠፉ ወይም የተበላሹ ሰነዶችን መከላከል
- ሰነድ ለሚፈልጉ ሠራተኞች ተገቢውን መረጃ መስጠት እና የተጠየቁ ፋይሎችን ፈልጎ ማቅረብ
- የተወሰዱ ፋይሎችን መመዝገብ እና መከታተል
- ሰነዶችን በኮምፒውተር መመዝገብ እና Scan አድርጎ በዲጂታል መልክ ማስቀመጥ
- የመረጃ ቋት (Database) ማዘመን
- የገቢና የወጪ ደብዳቤዎች እንዲሁም ወርሃዊና ዓመታዊ ሪፖርት ማዘጋጀትና ማቅረብ
- የሰነዶችን እንቅስቃሴ መከታተል
- የድርጅቱን ሚስጥራዊ መረጃ መጠበቅ እና በጊዜና በኃላፊነት ሥራን ማከናወን
- ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር በትብብር መሥራት
- የመዝገብ ቤቱን ሥራ በሥርዓት ማስኬድ እና ለቀጥተኛ ኃላፊ ተጠሪ መሆን
መስፈርቶች
- የትምህርት ደረጃ፡ ዲፕሎማ (Diploma)
- የሥራ ልምድ፡ ጀማሪ (Junior)
- ክህሎት፡ Customer Acquisition & Retention
- የቅጥር ሁኔታ፡ በቦታው ተገኝቶ የሚሰራ (Onsite) - ሙሉ ጊዜ
- ክፍት የሥራ ቦታ ብዛት፡ 2