የቅርንጫፍ ሱፐርቫይዘር
ስለ ሥራው
የቅርንጫፍ ሱፐርቫይዘር በቦሌ መድኃኒአለም፣ ቦሌ ቡልቡላ እና ካዛንቺስ ለሚገኙ ቅርንጫፎች አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ለመምራትና ለማስተባበር የሚፈለግ ክፍት የሥራ መደብ ነው። የተፈላጊ ሠራተኞች ብዛት 5 ነው።
ኃላፊነቶች
- የቅርንጫፉን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ መምራት፣ ማስተባበርና መቆጣጠር
- የአስተዳደር፣ የኦፕሬሽንና የምግብና መጠጥ አገልግሎት ሥራዎችን መከታተልና ማስተዳደር
- የቅርንጫፉ አገልግሎቶች በተቀላጠፈና በተሳለጠ ሁኔታ መሰጠታቸውን ማረጋገጥ
- የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም መከታተልና የድርጅቱ ፖሊሲዎችና ሥነ-ሥርዓቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ
- የደንበኞችን ፍላጎትና ቅሬታ በመከታተል አጥጋቢ መፍትሔ መስጠት
- የሥራ ቦታው ንጽህና፣ ደህንነትና ሥርዓት መጠበቁን ማረጋገጥ
- በሥራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መለየትና ተገቢ መፍትሔ መስጠት
- ከሚመለከታቸው የዘርፍ ኃላፊዎች ጋር መተባበርና በሥራ ኃላፊነቱ መሠረት ሪፖርት ማቅረብ
መስፈርቶች
- በቱሪዝም እና ሆቴል ማኔጅመንት ዲፕሎማ
- ከ2 እስከ 5 ዓመት አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ
የማመልከቻ ሂደት
አመልክት/ቺ የሚለውን ይጫኑ። የሥራ ቦታ ቦሌ መድኃኒአለም፣ ቦሌ ቡልቡላ እና ካዛንቺስ ሲሆን የማመልከቻው ማብቂያ ቀን November 10, 2026 ነው።