ትራክተር ኦፕሬተር
Minaye PLC
How to Apply
ስለ ሥራው
በሚናዬ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስር በሚገኘው የኤፍ ኤን (FN) የተቀናጀ እርሻ ልማት ውስጥ የትራክተር ኦፕሬተሩ የመሬት ዝግጅት፣ ተከላ፣ ክስካስ፣ የኬሚካል ርጭት፣ ትራንስፖርት እና ሌሎች የሜካናይዝድ እርሻ ስራዎችን ለመደገፍ ትራክተሮችን እና የእርሻ ማሽነሪዎችን በአስተማማኝና በብቃት የማንቀሳቀስ ሚና ይኖረዋል።
ኃላፊነቶች
- ትራክተሮችን እና ተያያዥ መሳሪያዎችን (ማረሻ፣ መክሰክሻ፣ መትከያ፣ መርጫ) በመጠቀም ተገቢውን የግብርና ስራ ማከናወን
- የትራክተሩን መደበኛ ፍተሻ እና መሰረታዊ ጥገና ማከናወን
- የሜካኒካል ብልሽቶች ሲያጋጥሙ ወዲያውኑ ለቅርብ ኃላፊ ሪፖርት ማድረግ
- በእርሻ ወቅት የማሽነሪዎችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ አጠቃቀም ማረጋገጥ
- እንደ አስፈላጊነቱ የግብዓት እና የቁሳቁስ ማጓጓዝ ስራዎችን ማገዝ
- ማሽን በማይሰራበት ወቅት በቅርብ ኃላፊ በሚሰጡ ሌሎች የስራ ምድቦች ላይ መሳተፍ
- የትራክተር ቁልፍ በኃላፊነት መያዝ እና እንደ አስፈላጊነቱ ለቅርብ ኃላፊ ማስረከብ
- የነዳጅ እና መለዋወጫ እቃዎችን ፈርሞ መቀበልና በኃላፊነት መያዝ
- የተመደቡ መሳሪያዎችን ንጽህና እና ትክክለኛ አያያዝ መጠበቅ
- የደህንነት ሂደቶችን እና የእርሻ ስራ መመሪያዎችን መከተል
መስፈርቶች
- የታደሰ የትራክተር ኦፕሬተር ፈቃድ ወይም ተዛማጅ የምስክር ወረቀት (Certificate)
- በግብርና ማሽነሪዎች አሰራር ላይ ቢያንስ 2 ዓመት የስራ ልምድ
- ለመደበኛ እና ጥቃቅን ጥገናዎች መሰረታዊ የሜካኒካል እውቀት (MRO)
- በከፍተኛ የእርሻ ወቅት ረጅም ሰዓታት የመስራት ዝግጁነት
- ኃላፊነት የሚሰማው፣ ደህንነትን የሚጠብቅ እና ጥሩ የመግባባት ችሎታ ያለው
እንዴት ማመልከት ይቻላል
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች አስፈላጊውን የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ በኢሜል አድራሻችን Talentaquisitionminaye@gmail.com መላክ ትችላላችሁ።