ጉዳይ አስፈጻሚ
Inayaz Construction
ስለ ሥራው
ኢናያዝ ኮንስትራክሽን እና ማቴሪያል ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ቀልጣፋ፣ ንቁ እና ከፍተኛ የማደራጀት ብቃት ያለው የጉዳይ አስፈፃሚ በቋሚነት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል። ይህ የሥራ መደብ በቢሮ ውስጥ የደንበኞችን መረጃ እና የድርጅቱን ጉዳዮች የማስተዳደር እንዲሁም በውጭ ያሉ የመንግሥትና የግል ተቋማት ጉዳዮችን አጣጥሞ የመስራት ኃላፊነትን ያካትታል።
ኃላፊነቶች
- በድርጅቱና በተለያዩ የመንግሥት ወይም የግል ተቋማት (እንደ ገቢዎች፣ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ባንኮች፣ ወዘተ) መካከል ያሉ ጉዳዮችን በቅርበት መከታተልና ማስፈጸም
- የንግድ ፈቃድ ማደስ፣ የግብርና ታክስ ፋይሎችን ማስተካከል እና ተያያዥ ጉዳዮችን መፈጸም
- የድርጅቱን የውሃ፣ መብራት፣ ስልክ እና ሌሎች መሠረታዊ ክፍያዎችን በወቅቱ መፈጸም
- በባንክ በኩል የሚከናወኑ የገንዘብ ማስገባት፣ የሰነዶች ማድረስና መቀበል ሥራዎችን በኃላፊነት ማከናወን
መስፈርቶች
- በማኔጅመንት፣ በሕግ፣ በአስተዳደር ወይም በተዛማጅ መስክ ዲፕሎማ ወይም ሰርተፊኬት
- ከ 2 እስከ 4 ዓመት በጉዳይ አስፈጻሚነት የሠራ (ይመረጣል)
- ፆታ፡ ወንድ
- የሥራ ቦታ፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ
- ከፍተኛ ንቁነት፣ መልካም የኮሚዩኒኬሽን ችሎታ እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር የመደራደርና የማስፈጸም ብቃት
- ሙሉ በሙሉ የታመነ፣ በስነ-ምግባሩ ምስጉን እና የጠራ ስም ያለው
- ያለምንም ማስታወሻ እና ማሳሰቢያ የተሰጡ ትእዛዞችን በፍጥነት እና በሰዓቱ የመፈጸም አቅም ያለው
- በኤክሴል (Microsoft Excel)፣ በሞባይል ባንኪንግ (ቴሌብር / CBE Birr) እና በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ በቂ እውቀት ያለው
- በአማርኛ ቋንቋ ጥሩ የጽሁፍ እና የንግግር ችሎታ ያለው (መሰረታዊ የእንግሊዝኛ እውቀት ያለው ይመረጣል)