S
ቴብል ሶዉ ማሽኒስት (ለፈርኒቸር)
SHI-FAM TRADING PLC
ስለ ስራው
SHI-FAM TRADING PLC በቦሌ ጃክሮስ ሮቤራ ካፌ አጠገብ ለሚገኘው የስራ ቦታ ሁለት የቴብል ሶዉ ማሽኒስቶችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
የስራ ኃላፊነቶች
- በቴብል ሶዉ ማሽን ላይ የተለያዩ MDF ሰሌዳዎችን በሚሰጠው ዲዛይን መሰረት መቁረጥ፣ መሰንጠቅ፣ ግሩቭ ማውጣት እና የተለያዩ ጆይንቶችን መስራት
- የማሽን መለኪያዎችን፣ ዲዛይን እና ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን በማንበብና በመረዳት መስራት
- ከሰራተኞች እና ከኃላፊዎች ጋር ተግባብቶ መስራት
መስፈርቶች
- የትምህርት ደረጃ፡ TVET
- ከሁለት ዓመት በላይ በፈርኒቸር ማሽኒስት (ቴብል ሶዉ) ላይ የስራ ልምድ ያለው/ላት
- የማሽን ቁጥጥርና ጥገና፣ የስራ ቦታ ደህንነት እና የጊዜ አጠቃቀም ክህሎት
- ዋስ/ተያዥ ማቅረብ የሚችል/ት
- ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መስራት የሚችል/ት
ጥቅማ ጥቅሞች
- ደመወዝ፡ በስምምነት
እንዴት ማመልከት ይቻላል
የስራ ልምድ ያላችሁ አመልካቾች ለተጨማሪ መረጃ በ 0910662428 መደወል ትችላላችሁ።