የጥበቃ ሰራተኛ
GET-HAB WOOD, METAL & ALUMINIUM
ስለ ስራው
GET-HAB WOOD, METAL & ALUMINIUM ድርጅት ክፍት በሆነው የጥበቃ ሰራተኛ የስራ መደብ ላይ ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ክፍት የስራ መደቦች ብዛት 4 ሲሆን የስራ ቦታው አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ ነው።
የስራ ኃላፊነቶች
- የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓትን አክብሮ በኃላፊነት መስራት
- ሰራተኞች ሲገቡና ሲወጡ በታማኝነት መፈተሽ
- የድርጅቱን ንብረት ከተረኛ ጥበቃ ጋር አንድ በአንድ ፈትሾ መረከብ እና ማስረከብ
- ሙሉ የግቢውን ደህንነትና የተቀመጡ ንብረቶች በንቃት መጠበቅ
- ድርጅቱ በሚያወጣው የፈረቃ (ሽፍት) ፕሮግራም መሰረት መስራት
- ሌሎች በድርጅቱ የሚሰጡ ተዛማጅ ስራዎችን በአግባቡ መወጣት
መስፈርቶች
- በጥበቃ ስራ ቢያንስ 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው
- በውትድርና የሰለጠነ ወይም በጥበቃ ስራ ላይ ስልጠና የወሰደ
- እድሜው ከ32 እስከ 40 ዓመት የሆነ
- የድርጅት ሰራተኛ የሆነ የዋስትና ደብዳቤ አጽፎ ዋስ ማቅረብ የሚችል
- ለጎሮ፣ ለመብራት ኃይል፣ ለጃክሮስ እና ለአካባቢው ቅርብ የሆነ
- ከሰራተኞች እና ከኃላፊዎች ጋር ተግባብቶ መስራት የሚችል
- 2ቱ ሰራተኞች 24 ሰዓት ሰርተው 24 ሰዓት እረፍት መስራት የሚችሉ፣ ሌሎቹ 2 ደግሞ ሙሉ ወር የቀን ከጠዋቱ 12:30 እስከ 11:30 እንዲሁም 15 ቀን የማታ ከ11:30 እስከ ንጋቱ 12:30 መስራት የሚችሉ
የማመልከቻ መንገድ
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910662428 መደወል ትችላላችሁ። አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ጃክሮስ።