ሸ
TikTok Live ልብስ አስተዋዋቂ
ሸማቴክስ
ስለ ሥራው
ሸማቴክስ የወንድ አልባሳት መሸጫ ድርጅት ሲሆን በሶሻል ሚዲያ አልባሳትን የሚያስተዋውቅ ጠንካራ፣ ቀልጣፋና ትጉህ የቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት (TikTok Live) ልብስ አስተዋዋቂ ይፈልጋል። የሥራ ሰዓቱ ከጠዋቱ 3:30 እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ነው።
ኃላፊነቶች
- በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት (TikTok Live) እና ማህበራዊ ሚዲያ አልባሳትን በንቃት ማስተዋወቅ
- ደንበኞችን በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ
መስፈርቶች
- የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ላት (በኢንጅነሪንግ የተመረቁ አመልካቾች ይበረታታሉ)
- በዘርፉ በቂ ልምድ ያለው/ላት
- ጠንካራ፣ ቀልጣፋ፣ ትጉህ እና ኃላፊነት የሚሰማው/ት
- ከመንግስት ወይም ከባንክ ሰራተኛ መስሪያ ቤት የዋስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ተያዥ ያለው/ላት
- መገናኛ ወይም ጀሞ አቅራቢያ የሚኖር/የምትኖር
የማመልከቻ መንገድ
ለሥራ ማመልከት የምትፈልጉ በቴሌግራም @Shematex (Telegram Channel) ማመልከት ትችላላችሁ።