የማሽነሪ ግዥና የፋብሪካ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ኃላፊ
Haylo Ethio Trading PLC
ስለ ሥራው
ሃይሎ ኢትዮ ትሬዲንግ (Haylo Ethio Trading PLC) የምግብ ፋብሪካውን ለማስፋፋት፣ ማሽነሪዎችን ከውጭ አገር ለማስመጣት፣ በአገር ውስጥ አምራቾችን ለማፈላለግ እና ማሽነሪዎችን ተክሎ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚችል ብቁ የማሽነሪ ግዥና የፋብሪካ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ኃላፊ ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- ለፋብሪካው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችን መለየትና ከቱርክ፣ ከአውሮፓና ከቻይና አምራቾች ማፈላለግ
- በኢትዮጵያ ውስጥ ማሽነሪዎችን ሊያመርቱ የሚችሉ የአካባቢ ባለሙያዎችን፣ የኢንጂነሪንግ ድርጅቶችንና የማሽን ሠሪ ዎርክሾፖችን ማፈላለግና ሥራውን ማስተባበር
- የማሽነሪዎችን ዋጋ፣ ጥራት፣ አቅምና የሥራ ብቃት በማወዳደር የግዥ ምክረ ሐሳብ ማቅረብ
- ከባንክ ጋር የማሽነሪ ብድር ሂደትን መከታተል
- ማሽነሪዎችን በፋብሪካው ማስገጠም፣ ማስፈተሽና ወደ ሥራ ማስገባት
መስፈርቶች
- የመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's Degree) እና ከፍተኛ (Senior) የሥራ ልምድ ያለው
- በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ በኢንዱስትሪ ማሽነሪ ወይም በፋብሪካ ማሽነሪ ግዥና ተከላ ላይ ተግባራዊ ልምድ ያለው
- ከውጭ አገር ማሽነሪ የማስመጣትና የኢትዮጵያን የጉምሩክ ሂደት የሚያውቅ
- በአገር ውስጥ የማሽን ሠሪዎችን ማፈላለግና የማምረት ሥራን ማስተባበር የሚችል
- የብድር ሂደቶችን፣ የውጭ አገር አቅራቢዎችንና የፕሮጀክት ሂደቶችን መከታተል የሚችል
- በማሽን ኦፕሬሽን፣ ተከላ፣ ጥገና እና ዲዛይን ላይ ክህሎት ያለው
- ታማኝ፣ ተግባራዊ፣ ችግር ፈቺና ሥራን ከመጀመሪያ እስከ ፍጻሜ የሚያስፈጽም