Y
Senior Sales Representative
Yona Yeajeyet Trading PLC
ስለ ሥራው
ዮና የአጅየት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለፈርኒቸር ምርቶችና አገልግሎቶች ሽያጭ ከፍተኛ የሥራ ልምድ ያለው ባለሙያ በሙሉ ጊዜ (Hybrid) መቅጠር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ (በተለይም አዲስ በተጠናቀቁ የሪል ስቴት ፕሮጀክቶች፣ ኮንስትራክሽኖች፣ ቢሮዎች እና መኖሪያ ቤቶች) የፈርኒቸር ፍላጎት ያላቸውን ደንበኞች መለየት እና ማግኘት
- ከሪል ስቴት አልሚዎች፣ ከኮንስትራክሽን ባለቤቶች፣ ከአርክቴክቶች እና ከቤት ባለቤቶች ጋር ቀጥተኛ የንግድ ግንኙነት መመሥረት
- የድርጅቱን የፈርኒቸር ምርቶች እና አገልግሎቶች በጥራት ለደንበኞች ማስተዋወቅ እና ማስረዳት
- የደንበኞችን ፍላጎት በመረዳት የፈርኒቸር ትዕዛዞችን ማምጣት እና ሽያጭ ማጠናቀቅ
- አዳዲስ የተጎበኙ ቦታዎችን፣ የተገኙ ደንበኞችን እና የሽያጭ ሂደቶችን ሁኔታ ለድርጅቱ በየጊዜው ሪፖርት ማድረግ
መስፈርቶች
- የመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's Degree)
- ከፍተኛ የሥራ ልምድ (Senior level)
- የማስተዋወቅና የኮሙኒኬሽን ችሎታ (Communication and Marketing Management skills)