H
የሱቅ ሰራተኛ
Haylo Ethio Trading PLC
ስለ ሥራው
Hay’lo Ethiopia በቤተል ቅርንጫፍ በሙሉ ጊዜ ቅጥር በትጋት፣ በታማኝነት እና በኃላፊነት መስራት የምትችል ሴት የሱቅ ሰራተኛ መቅጠር ይፈልጋል። የሥራ ሰዓቱ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ነው።
ኃላፊነቶች
- ደንበኞችን በጥሩ ሁኔታ ማስተናገድ እና ስለ ምርቶች መረጃ መስጠት
- ምርቶችን መሸጥ እና የዕለት ሽያጭን በትክክል መመዝገብ
- ገንዘብና የባንክ ዝውውር ክፍያዎችን በትክክል መቆጣጠር
- የሱቁን እቃዎች ብዛት መከታተል እና የእቃ እጥረትን ሪፖርት ማድረግ
- ሱቁን ንጹህ፣ የተደራጀ እና ለደንበኞች ምቹ ማድረግ
መስፈርቶች
- የትምህርት ደረጃ የቴክኒክና ሙያ (TVET) ምሩቅ
- መካከለኛ የሥራ ልምድ ያለው (በሽያጭ ዘርፍ ልምድ ያላት ቅድሚያ ይሰጣታል)
- ጥሩ የግንኙነት እና የደንበኛ አያያዝ ችሎታ
- የሂሳብ ቁጥር መቁጠርና መዝገብ የመያዝ ችሎታ
- በሰዓት የምትገኝ፣ ታማኝ፣ ኃላፊነት የምትወስድ እና ለመማር ፈቃደኛ የሆነች