P
Laundry Customer Service
Private Client
ስለ ስራው
ለላውንድሪ ንግዳችን ደንበኞችን በአክብሮት፣ በፍጥነት እና በጥራት የሚያስተናግድ ሰራተኛ እንፈልጋለን። ተቀጣሪው ደንበኞችን በመቀበል፣ ማሽኖችን እንዲጠቀሙ በማገዝ እንዲሁም ሙሉ የልብስ ማጠብ፣ ማድረቅ እና ማጠፍ አገልግሎት በመስጠት ይሰራል/ትሰራለች።
ኃላፊነቶች
- ደንበኞችን በደስታ መቀበል፣ ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት እና ጽዱና ምቹ አካባቢ መፍጠር
- ደንበኞች የማጠቢያ እና ማድረቂያ ማሽኖችን በትክክል እንዲጠቀሙ ማሳየት እና ቀላል ችግሮች ሲያጋጥሙ መፍትሔ መስጠት
- ደንበኞች የሚተውትን ልብስ ተረክቦ መመዝገብ፣ በታዘዘው መመሪያ መሰረት ሙሉ በሙሉ ማጠብ፣ ማድረቅ እና ማጠፍ እንዲሁም ሲጠናቀቅ ማሳወቅ
- የእድፍ ምልክት ያላቸውን ልብሶች መመርመር እና ተገቢውን የጽዳት ወይም የቅድመ-ማጠብ ምክር መስጠት
- የማጠቢያ ቦታውን፣ ማሽኖችን፣ የልብስ ማጠፊያ ጠረጴዛዎችን እና የደንበኞች መቀመጫ ቦታን ሁልጊዜ ጽዱ ማድረግ
መስፈርቶች
- የትምህርት ደረጃ፦ የሁለተኛ ደረጃ (High School)
- የስራ ልምድ፦ ጀማሪ (Entry level)
- ጥሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ክህሎት ያለው/ላት
- ለቡልቡላ ቅርብ የሆነ/ች