Fast Food and Fresh Juice Chef
Bloom Juice & Burger
ስለ ሥራው
የብሉም ጁስ ኤንድ በርገር ሼፍ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የተለያዩ የበርገር አይነቶች፣ ፒዛ፣ ሻዋርማ፣ ፈጢራ፣ ሳንድዊቾች፣ ሰላጣዎች፣ የባህል የጾም ምግቦች እንዲሁም ትኩስ የተፈጥሮ ጁሶችን በጥራት እና በንጽህና የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት። የሥራ ቦታው በላፍቶ ኬብሮን አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ የደንበኞችን እርካታ ማረጋገጥ እና የምግብ አዘገጃጀትን ማበልጸግ ዋና ዓላማው ያደረገ ነው።
ኃላፊነቶች
- የተለያዩ የበርገር አይነቶችን (ክላሲክ፣ ቺዝ፣ ደብል፣ ክሪስፒ፣ ቪጂ እና ስፔሻል ብሉም በርገር) እና ተጓዳኝ ሶሶችን ማዘጋጀት
- የፒዛ ሊጥ ማዘጋጀት እና የተለያዩ የፒዛ አይነቶችን በጥራት መጋገር
- ጥፍጥናቸው የጠበቁ የሻዋርማ ጥቅልሎችን እና ትኩስ የፈጢራ አይነቶችን ማዘጋጀት
- የተለያዩ ክለብ ሳንድዊቾችን፣ ቶስቶችን እና ትኩስ ሰላጣዎችን ማዘጋጀት
- ያለ ስጋ የሚዘጋጁ ባህላዊ የጾም ምግቦችን (ፍርፍር፣ ሽሮ፣ በያይነቱ፣ ድንች በቲማቲም) በጥሩ ጣዕም ማብሰል
- ልዩ ልዩ የተፈጥሮ ፍሩት ፓንች፣ ስፕሪስ፣ ትኩስ የፍራፍሬ ጁሶችን፣ የፍራፍሬ ሰላጣ እና ስሙዚዎችን ማዘጋጀት
- አዳዲስ የምግብና የመጠጥ አዘገጃጀት መመሪያዎችን (Recipes) መፍጠር እና አቀራረብን ማሳመር
- የወጥ ቤቱን፣ የማብሰያና የጁስ መጭመቂያ ማሽኖችን ንጽህና እና የምግብ ደህንነት ደንቦችን በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ
መስፈርቶች
- በምግብ ዝግጅት (Culinary Arts / Food Preparation) ወይም በተመሳሳይ ሙያ ሰርተፊኬት
- በበርገር፣ ፒዛ፣ ፈጣን ምግቦች እና ጁስ ዝግጅት ላይ ቢያንስ 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ
- አዳዲስ የምግብና የጁስ አቀራረቦችን እና ጣዕሞችን የመፍጠር የፈጠራ ችሎታ
- አዳዲስ ሬሲፒዎችን የማዘጋጀት እና የምግብ አዘገጃጀት መመሪያን የማበልጸግ ችሎታ
- ፈጣን፣ ንቁ፣ ጫናን ተቋቁሞ የመስራት እና አዳዲስ ነገሮችን የመማር ዝግጁነት
እንዴት ማመልከት ይቻላል
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ሲቪያችሁን (CV) እና የትምህርት/የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን እስከ ጥቅምት 25 ድረስ በ 0925873168 ወይም በ telegram መላክ ትችላላችሁ።