የክወና እና ምስላዊ ጥበባት (PVA) መምህር
ንሥር ትምህርት ቤት
ስለ ሥራው
ንሥር ትምህርት ቤት የታችኛ ደረጃ ተማሪዎችን የተፈጥሮ ፈጠራ፣ ጥበባዊ ስሜት እና የሰውነት ቅንጅት የሚያሳድግ የክወና እና ምስላዊ ጥበባት (PVA) መምህር ይፈልጋል። የሥራው ዋና ዓላማ ሙዚቃን፣ ትወናን፣ ባህላዊ ውዝዋዜን እና ምስላዊ ጥበባትን በማቀናጀት የተማሪዎችን በራስ መተማመን መገንባት እና ስሜታቸውን በነጻነት እንዲገልጹ ማስቻል ነው።
ኃላፊነቶች
- በፒቪኤ ካሪኩለም መሠረት ሳምንታዊ እና ዕለታዊ የትምህርት ዕቅድ (Lesson Plan) ማዘጋጀት
- የሙዚቃ፣ የትወና፣ የውዝዋዜ እና የስዕል ትምህርቶችን በተግባር የተደገፈ እና አሳታፊ በሆነ መንገድ ማቅረብ
- የተማሪዎችን የስሜት፣ የፈጠራ እና የክህሎት ዕድገት መከታተል እና ምዘና ማድረግ
- በትምህርት ቤቱ ልዩ ልዩ በዓላት ላይ የተማሪዎችን የጥበብ፣ የሙዚቃ እና የቲያትር ትርኢቶች ማዘጋጀት
- ከአካባቢ ቁሳቁሶች እና አነስተኛ ወጪ ከሚጠይቁ ነገሮች የማስተማሪያ ግብአቶችን ማዘጋጀት
መስፈርቶች
- በቲያትር/ክወና ጥበባት፣ በሙዚቃ፣ በስዕል (Fine Arts) ወይም በተዛማጅ የትምህርት ዘርፍ ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ (ወይም በተግባር የተረጋገጠ ልዩ የጥበብ ክህሎት)
- ከህፃናት ወይም ከታችኛ ደረጃ ተማሪዎች ጋር የማስተማር ወይም የመሥራት ልምድ ያለው/ላት ቢሆን ይመረጣል
- በሙዚቃ (መዝሙር፣ ሪትም ወይም መሠረታዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች)፣ በትወና እና በስዕል/እደ-ጥበብ ላይ በቂ ተግባራዊ ችሎታ
- የልጆችን ትኩረት የሚስቡ አጫጭር ተውኔቶችን እና የጥበብ ሥራዎችን የመፍጠር አቅም
- በክፍል ውስጥ ንቁ፣ ተጫዋች እና በሰውነት እንቅስቃሴ (Gestures) የታገዘ የማስተማር ስልት
- ክፍሉን በደስታና በስርዓት (በ WBT - Whole Brain Teaching ፕሮሲጀሮች) የመምራት ችሎታ
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አድራሻ፦ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ አዲስ አበባ (ከፈረማ ትምህርት ቤት አጠገብ)
ለማመልከት በቴሌግራም፦ @Nisirbusiness