የኦፕሬሽን አስተባባሪ
Not specified
ስለ ስራው
የኦፕሬሽን አስተባባሪው በፕሮጀክቱ ስር የሚገኙ የጥበቃ አባላትን ዕለታዊ ስራ ፈረቃ፣ ስምሪት እና አጠቃላይ የኦፕሬሽን እንቅስቃሴዎችን በበላይነት የመምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት ይኖርበታል።
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
- በፕሮጀክቱ ስር የሚሰሩ ከ700 በላይ የጥበቃ አባላትን ዕለታዊ ስራ ፈረቃ እና ስምሪት ማቀድ፣ ማስተካከል እና በበላይነት መከታተል
- ከዓለም አቀፍ ህጎች እና ከድርጅቱ SOP (መደበኛ የአሰራር ስርዓት) ጋር የተጣጣሙ ወቅታዊ የኦፕሬሽንና የክትትል ሪፖርቶችን ማዘጋጀት እና ማቅረብ
- የሰራተኞችን ስነ-ስርዓት፣ አፈፃፀም እና ተነሳሽነት መከታተል እንዲሁም የሚነሱ ቅሬታዎችን እና ክፍተቶችን በወቅቱ መፍትሄ መስጠት
- የሰራተኞች ምደባ፣ የቁጥጥር ስራዎች፣ የብቃት ማረጋገጫዎች እና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነቶችን በበላይነት መምራት
መስፈርቶች
- በኢንቨስትጌሽን፣ በወታደራዊ/ፖሊስ ሳይንስ፣ በማኔጅመንት ወይም በተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
- ከ5 እስከ 8 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ (በጥበቃ እና ደህንነት ወይም በከፍተኛ መጠን ሰራተኞችን በመምራት ዘርፍ)
- እንግሊዘኛ እና አማርኛ ቋንቋ መናገርና መፃፍ የሚችል/የምትችል
- ዕድሜ ከ30 እስከ 50 ዓመት
ጥቅማ ጥቅሞች
- ደመወዝ 50,000.00 ብር
- ቁርስ እና ምሳ
- የሰርቪስ አገልግሎት
- በስራ ላይ ለሚገጥም ጉዳትም ሆነ ሞት ኢንሹራንስ
- የሃዘን፣ የደስታ እና የዓመት ፈቃድ
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አመልካቾች መገናኛ ከአምቼ ጀርባ ጃፓን መኖሪያ መንደር በሚገኘው ቢሮአችን በአካል በመምጣት ማመልከት ይችላሉ።
የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን: October 30, 2026
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 0922464043 ይደውሉ።