የውል አስተዳደር ባለሙያ
ስለ ስራው
ድርጅቱ ክፍት በሆነው የውል አስተዳደር ባለሙያ የሥራ መደብ ላይ ብቁ ባለሙያ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- ከደንበኞች እና ከአገልግሎት ተቀባይ ተቋማት ጋር የሚደረጉ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ውሎችን ማዘጋጀት፣ መከታተል እና ማደስ
- MS Office (Word, Excel, Outlook) እና ኢሜል መጠቀም
- የውል ሰነዶችን በጥንቃቄ ማደራጀት፣ መመዝገብ እና በዘመናዊ መንገድ አደራጅቶ መያዝ
መስፈርቶች
- በህግ፣ በቢዝነስ አስተዳደር፣ በማኔጅመንት፣ በኮምፒውተር ሳይንስ ወይም በተዛማጅ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ
- ቢያንስ 2 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ
- በውል አስተዳደር፣ በህግ አገልግሎት ወይም በሰው ኃይል አስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም ዳታቤዝ ሲስተም ላይ የስራ ልምድ
- ዕድሜ ከ30 እስከ 55 ዓመት
- የሚፈለገው ብዛት፡ 1
ጥቅማ ጥቅሞች
- ደመወዝ፡ 20,300.00 ብር
- የሃዘን፣ የደስታ እና የዓመት ፈቃድ
- በስራ ላይ ለሚገጥም ጉዳትም ሆነ ሞት ኢንሹራንስ
- ቁርስ እና ምሳ
- የሰርቪስ አገልግሎት
የማመልከቻ መንገድ
አመልካቾች መገናኛ ከአምቼ ጀርባ ጃፓን መኖሪያ መንደር በሚገኘው ቢሮአችን በአካል በመምጣት ማመልከት ይችላሉ።
የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን፡ October 30, 2026
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡ 0922464043 ይደውሉ።