Electric Motorbike delivery driver
Private Client
Job Type: Onsite - Full Time
Experience: Intermediate
Vacancies: 5
Skills: Patient Transport
የዲሊቨሪ ሹፌር (Delivery Driver) የሥራ ማስታወቂያ
● የሥራ ድርሻ
የድርጅቱን ኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት በመንዳት ምግብ፣ ጥቅል ዕቃዎችና ሰነዶችን ለደንበኞች በፍጥነት፣ በጥንቃቄና በታማኝነት ማድረስ።
● የዋስትና መስፈርት
• ማን ዋስ መሆን ይችላል?በመንግሥት ወይም በታወቀ የግል ድርጅት የሚሠራና የሥራና የደመወዝ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤ ወይምሕጋዊ የቤት ወይም የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ያለው።
• በመንግሥት ወይም በታወቀ የግል ድርጅት የሚሠራና የሥራና የደመወዝ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤ ወይም
• ሕጋዊ የቤት ወይም የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ያለው።
• የዋሱ ግዴታ፦ ዋሱ አስፈላጊ ሰነዶችን ይዞ በአካል ወደ ድርጅቱ ቢሮ በመምጣት የዋስትና ቅጽ መፈረም አለበት።
• ተቀባይነት ያለው ዋስ ማቅረብ ግዴታ ነው።
● አስፈላጊ መስፈርቶች
• ትክክለኛ የመንጃ ፈቃድ ያለው።
• ኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌትን በደህንነትና በራስ መተማመን መንዳት የሚችል።
• የራሱ ስማርት ስልክ (Smartphone) ያለውና Google Maps መጠቀም የሚችል።
• የአዲስ አበባን መንገዶችና ሰፈሮች በደንብ የሚያውቅ።
• ታማኝ፣ ሰዓት አክባሪና ኃላፊነት የሚሰማው።
• የትራፊክ ሕጎችን የሚያከብርና የደንበኞችን ዕቃዎች በጥንቃቄ የሚይዝ።
• በዲሊቨሪ ወይም በሹፌርነት ሥራ ልምድ ያለው ቢሆን ይመረጣል።
● የሚሰጡ ጥቅማ ጥቅሞች
• ተመጣጣኝ ደመወዝ።
• ለሥራ የሚያስፈልገው ኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት ከድርጅቱ ይቀርባል።
• በድርጅቱ የሥራ ሥርዓትና ደንብ መሠረት የሥራ እድል።
ማሳሰቢያ፦ ትክክለኛ የመንጃ ፈቃድና ተቀባይነት ያለው ዋስ ማቅረብ የግድ ነው።