ጥበቃ
Not specified
ስለ ሥራው
ድርጅቱ 40 ክፍት የሥራ መደቦች ላይ የጥበቃ ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- የድርጅቱን ሕንፃ፣ ንብረትና እቃዎች ደህንነት መጠበቅ
- ወደ ድርጅቱ የሚገቡና የሚወጡ ሰዎችን መቆጣጠር
- የድርጅቱን የመግቢያና መውጫ በሮች መቆጣጠር
- አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችንና የደህንነት ችግሮችን ለኃላፊው ማሳወቅ
- የድርጅቱን የደህንነት ደንቦችና መመሪያዎች ማክበር
- የድርጅቱን ንብረት ያለ ፈቃድ ከግቢው እንዳይወጣ መቆጣጠር
- በሥራ ሰዓት የሚከሰቱ አደጋዎችንና ያልተለመዱ ክስተቶችን መመዝገብና ሪፖርት ማድረግ
- በተመደበው የሥራ ሰዓት በታማኝነትና በኃላፊነት ማገልገል
- የሥራ ቦታውን ንጽህናና ሥርዓት መጠበቅ
- ከሥራው ጋር የተያያዙ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን
መስፈርቶች
- 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ወይም ከቴክኒክና ሙያ በማንኛውም መስክ የሰለጠነ
- ለወንድ አመልካቾች ብቻ (ዕድሜ ከ25 እስከ 40 ዓመት)
- ወታደር የነበሩ እና ስንብት ያላቸው
ጥቅማ ጥቅሞች
- ወርሃዊ ደመወዝ፡ 10,521.74 ብር
- ያልተጣራ የትራንስፖርት አበል፡ 2,630.44 ብር
- የሃዘን፣ የደስታ እና በስራ ላይ ለሚገጥም ጉዳትም ሆነ ሞት ኢንሹራንስ
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አመልካቾች መገናኛ ከአምቼ ጀርባ ጃፓን መኖሪያ መንደር በሚገኘው ቢሮአችን በአካል በመምጣት ማመልከት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡ 0922464043 ይደውሉ፡፡
የማመልከቻ መጨረሻ ቀን፡ October 28, 2026