Receptionist
Private Client
Job Type: Onsite - Full Time
Education: Diploma
Experience: Intermediate
Vacancies: 1
Skills: Persuasive Communication, Professional Ethics, Professional Responsibility, Professionalism, Communication, Professional Networking
የሥራው አጠቃላይ መግለጫ
ኢንግሊሽ ጉሩ ኢንስትቲዩት (English Guru Institute) ለተቋማችን የፊት ለፊት አስተናጋጅ (Receptionist) ሆና የምታገለግል፣ ቀልጣፋ፣ ተግባቢ እና ስነ-ስርዓት ያላት ሴት የሪሴፕሽንነት ይፈልጋል። በዚህ የሥራ መደብ ላይ የሚመደቡት ሰራተኛ የተቋማችን መጀመሪያ ገጽታ በመሆን አዳዲስ እና ነባር ተማሪዎችን፣ ወላጆችን እና እንግዶችን በተለያየ ሁኔታ ያስተናግዳሉ፤ መረጃ ይሰጣሉ፣ እንዲሁም የቢሮውን የዕለት ተዕለት አስተዳደራዊ ስራዎች ያከናውናሉ።
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
የሪሴፕሽን እና የእንግዳ ተቀባይነት ስራዎች፡
እንግዶችን፣ ተማሪዎችን እና ወላጆችን በደስታ እና በትህትና የተቀበሉ ማስተናገድ።
የሪሴፕሽን አካባቢውን ሁልጊዜ ጽዳቱ የተጠበቀ፣ የተደራጀ እና ማራኪ ማድረግ።
መረጃ መስጠት እና ግንኙነት፡
ለሚደወሉ ስልኮች እና ለሚላኩ መልእክቶች (በቴሌግራም/ዋትስአፕ) ላይ ምላሽ መስጠት።
ስለ ትምህርት ዓይነቶች፣ የክፍል ፕሮግራሞች፣ የክፍያ ሁኔታዎች እና የምዝገባ ሂደት በአካል ለሚመጡና በስልክ ለሚጠይቁ ደንበኞች ሙሉ መረጃ መስጠት።
የተማሪዎች ምዝገባ እና አስተዳደራዊ ድጋፍ፡
አዳዲስ ተማሪዎችን ማስመዝገብ እና ሂደቱን ማጠናቀቅ።
የተማሪዎችን መረጃ፣ የስልክ አድራሻ እና የቁጥጥር መዝገቦችን በስርዓት መያዝ።
የትምህርት ክፍያዎችን መቀበል፣ መመዝገብ እና ደረሰኝ መስጠት።
የቢሮ ቅንጅት፡
ከመምህራን እና ከአስተዳደር ክፍሉ ጋር በመተባበር የህትመት እና የፕሮግራም ማስተካከያ ስራዎችን መደገፍ።
የቢሮ ዕቃዎችን እና የጽህፈት መሳሪያዎችን ክምችት መከታተል።
የሥራው መስፈርቶች
ጾታ: ሴት ብቻ
መኖሪያ ቦታ:
ለቡ ወይም ለለቡ ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ (ለቡ፣ መካኒሳ፣ ጃሞ፣ ኃይሌ Garment ወዘተ.)
ትምህርት ደረጃ:
በዲፕሎማ ወይም በባችለር ዲግሪ በማኔጅመንት፣ በሴክሬተሪያል ሳይንስ፣ በቢዝነስ አስተዳደር፣ በኮሙኒኬሽን ወይም በተዛማጅ ዘርፎች የተመረቀች።
የቋንቋ ችሎታ:
አማርኛ ቋንቋ በቃልም ሆነ በጽሁፍ በጥሩ ሁኔታ መናገር/መፃፍ የምትችል።
እንግሊዝኛ ቋንቋን በጥሩ ደረጃ መነጋገር እና መረዳት የምትችል።
የኮምፒውተር ችሎታ: መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት ያላት (Microsoft Office፣ Telegram እና Email አጠቃቀም)።
የግል ባህሪያት:
ጥሩ የደንበኛ አያያዝ እና የማስረዳት ችሎታ ያላት።
ታማኝ፣ ሰዓት የምታከብር እና ስራን በተደራጀ ሁኔታ የምታከናውን።
ተቋሙ የሚያቀርበው
ምቹ እና አበረታች የሥራ አካባቢ።
በስራ ልምድ እና በችሎታ ላይ የተመሰረተ ተወዳዳሪ ደሞዝ።
ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟዪ ከሆንሽ በ telegram @techgirl ላይ reception ብለሽ text አርጊልን