ረዳት ሼፍ
Mulmul Bakery
How to Apply
ስለ ስራው
ድርጅታችን 4 ረዳት ሼፎችን መቅጠር ይፈልጋል። ተቀጣሪዎች ለዋናው ሼፍ የምግብ ዝግጅት እገዛ የማድረግ እና የኩሽናውን ንጽህናና ጥራት የማስጠበቅ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል።
ኃላፊነቶች
- የምግብ ዝግጅት ስራዎችን ለዋናዉ ሼፍ በማገዝ ማከናወን
- የምግብ ዝግጅት ቦታዎችን፣ ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን ንጹህ ማድረግ
- የደንበኞችን የምግብ ትዕዛዝ በፍጥነትና በትክክል ማዘጋጀት
- የምግብ ንጽህናና የጤና ደህንነት መመሪያዎችን መተግበር
- የምግብ ግብዓቶችን አጠቃቀም መቆጣጠርና ብክነትን መቀነስ
- የምግብ ግብዓቶች ክምችት ሲያንስ ለኃላፊዉ ሪፖርት ማድረግ
- የግሉንም ሆነ የስራ ቦታ ንጽህና መጠበቅ
- የምግብ ጥራት እንዲጠበቅ የሚያስፈልጉ ሂደቶችን መከተል
- የድርጅቱን የስራ መመሪያ ማክበር
- የጋራ ስራዎችን በፈቃደኝነት ማከናወን
መስፈርቶች
- በተዛማጅ የትምህርት መስክ ዲፕሎማ
- 2 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ
- ተያዥ ማቅረብ የሚችል/ምትችል
እንዴት ማመልከት ይቻላል
ከላይ የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን በኢሜል አድራሻችን mulmulhr@gmail.com ወይም የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ሃያ ሁለት ቅርንጫፍ በሚገኘው ዋናው ቢሮ በስራ ቀናት ከሰኞ - አርብ ከ2፡00 እስከ 11፡00 እና ቅዳሜ እስከ 6፡00 በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማስታወሻ፡ አመልካቾች ተያዥ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
የማመልከቻ ማጠናቀቂያ ቀን፡ October 29, 2026