N
አካውንታንት
Not specified
ስለ ሥራው
ድርጅቱ ክፍት በሆነው የአካውንታንት የሥራ መደብ ላይ ብቁ የሆነች አመልካች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- የድርጅቱን የገቢና የወጪ ሂሳቦች መመዝገብና ማስተዳደር
- የዕለት የገንዘብ እንቅስቃሴዎችን መመዝገብና ማረጋገጥ
- የደረሰኞችን፣ የክፍያ ቫውቸሮችንና ሌሎች የሂሳብ ሰነዶችን ማዘጋጀትና ማረጋገጥ
- ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመትና ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት
- የድርጅቱን በጀት አፈጻጸም መከታተልና የወጪ ቁጥጥር ማድረግ
- የሂሳብ መዝገቦችና ሰነዶች በትክክል መያዛቸውንና በደህንነት መቀመጣቸውን ማረጋገጥ
- ለውስጥና ለውጭ ኦዲት የሚያስፈልጉ ሰነዶችንና መረጃዎችን ማዘጋጀት
- የድርጅቱን የፋይናንስ ፖሊሲዎችና የሂሳብ አሠራሮች መከተል
መስፈርቶች
- በአካውንቲንግ ዲፕሎማ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት
- ከ0 እስከ 5 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ
- የስራ መደቡ ለሴት አመልካቾች ብቻ የተፈቀደ
እንዴት ማመልከት ይቻላል
ጎፋ ገብርኤል አደባባይ ቅድስት አርሴማ ህንፃ አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በአካል በመቅረብ ማመልከት ይቻላል።
የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን: October 31, 2026
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251911224507 ይደውሉ።