Receptionist & Cashier
SHI-FAM TRADING PLC
Job Type: Onsite - Full Time
Education: Bachelor’s Degree
Experience: Expert
Vacancies: 2
Skills: Front Controller Pattern, Active Listening, Relationship Management, Customer Relationship Management, Communication
በጅም ቤት ዉስጥ በሪሰፕሽኒስት & በካሸሪነት ከ2 ዓመት በላይ የስራ ልምድ ያላትና ለጃክሮስ ቅርብ የሆነች አመልካች ብቻ ለበለጠ መረጃ 0910662428 መደወል ይቻላል፣
የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦
• የካሸሪነት የስራ ልምድ ያላትና ደረሰኝ በካሽ ሪጅስተር መቁረጥና አታችመንት መስራት የምትችል፣
• የካሸሪ እና የሪሰፕሽኒስት የስራ ልምድ ያላት፣
• ጥሩ የግንኙነት ችሎታ፣ ትህትና፣ ታማኝነት፣ የደንበኛ አገልግሎት ብቃት፣
• የኮምፒውተር እውቀትና በቡድን የመስራት ችሎታ፣
• የድርጅታችንን ደንበኞች በሙያዊና በተግባቦት ማስተናገድ የምትችል፣
• የአባልነት ምዝገባና ክፍያን በመከታተልና በመቆጣጠር ማስተዳደር የምትችል፣
• የደንበኞችን ጥያቄና ቅሬታ በመቀበል በወቅቱ መፍትሄ እንዲሰጥበት ማድረግ የምትችል፣
• ፈጣንና ተግባቢ የሆነች ፣
• የእለት ተዕለት የሪሰፕሽን ሥራዎችን በማስፈጸም ብቁ የስራ ልምድ እና ችሎታ ያላት፣
• ለጃክሮስ ቅረብ የሆነች እና ከሰኞ እስከ እሁድ ከንጋት 12፡00 እስከ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ መስራት የምትችል በሳምንት አንድ ቀን እረፍት አለዉ።
• የሚሰጠዉን ፈተና ካለፈች በኋላ ዋስ/ተያዥ ማቅረብ የምትችል፣
የስራ ኃላፊነትና ተግባር
• የስራ ልምድ በሪሰፕሽኒስት የሰራችና የስራ ልምድ ማቅረብ የምትችል፣
• የጂምና ስፓ ደንበኞችን በአክብሮት፣ በፈገግታና በሙያዊ አቀራረብ መቀበል፣
• ለአዲስና ለነባር ደንበኞች ስለ ጂም፣ ስፓ፣ ሳውና፣ ስቲምና ሌሎች አገልግሎቶች ትክክለኛ መረጃ መስጠት፣
• የአባልነት ምዝገባ፣ እድሳትና ማቋረጥ ሂደትን በትክክል ቁጥጥር በማድረግ ማስተናገድ፣
• የደንበኞችን የአባልነት መረጃ፣ የመግቢያ መዝገብና የክፍያ መረጃ በአግባቡ መመዝገብ፣
• የደንበኛ መረጃ በትክክል መመዝገብና አደራጅቶ መያዝ፣
• የደንበኞችን የስልክ ጥሪ፣ መልዕክትና ጥያቄ መቀበልና ተገቢውን ምላሽ መስጠት፣
• የጂምና ስፓ የቀጠሮ ሥርዓትን ማስተዳደርና ቀጠሮዎችን በትክክል መመዝገብና ለሚመለከተዉ አካል በማሳወቅ መስራት፣
• የደንበኞችን ቅሬታና አስተያየት በትዕግሥት መቀበልና አስፈላጊ ሲሆን ለኃላፊ ማሳወቅና በወቅቱ እንዲፈታ ማድረግ፣
• የአባልነት ፓኬጆችን፣ ዋጋዎችንና የልዩ ቅናሽ ፕሮግራሞች ሲኖር ለደንበኞች ማስረዳት፣
• የደንበኛ ክፍያዎችን በድርጅቱ የክፍያ ሥርዓት መሠረት መቀበልና ደረሰኝ መስጠት፣
• የጂምና ስፓ መቀበያ ቦታ ንጹህ ለደንበኞች ምቹ ማድረግ፣
• ጥሩ የደንበኛ አያያዝ ስርዓቶችን በመከተል ደንበኛን በአክብሮት ማስተናገድ፣
• የደንበኞችን የግል መረጃና የክፍያ መረጃ በሚስጥር መጠበቅ፣
• ከPersonal Trainer፣ Spa Therapist፣ የጽዳት ሰራተኞችና ከሌሎች ኃላፊዎች ጋር በመሆን በጋር በቅርበት መስራት፣
• የጂምና ስፓ የዕለት ተዕለት ሥራ ሁኔታን መከታተልና ችግር ሲፈጠር ወዲያውኑ ለኃላፊ ማሳወቅ፣
• የደንበኛ እርካታን ለማሻሻል ፈጣን፣ ትህትና ያለውና ሙያዊ አገልግሎት መስጠት፣
• የዕለት የገቢ፣ የአባላትና የአገልግሎት ሪፖርት ማዘጋጀት፣
• የጂምና ስፓ የውስጥ ደንብ፣ የደህንነት መመሪያና የሥራ ሥነ-ምግባር መከተልና አክብሮ መስራት፣
• ሌሎች በኃላፊ የሚሰጡ ከሥራው ጋር የተያያዙ ተግባራትን በኃላፊነት ተቀብሎ መፈጸም፣
የትምህርት ዝግጅት
• በአካዉንቲንግ ፣ በአካዉንቲንግ & ፋይናንስ ፣ ማኔጅመንት እና በተመሳሳይ የት/ት ደረጃ በድግሪ የተመረቀች፣
የስራ ልምድ
• በጅምና ስፓ ላይ የሰራች ወይም በተመሳሳይ ተቋም ላይ ከሁለት(2) ዓመት በላይ በካሸሪና በሪሰፕሽን ላይ የስራ ልምድ ያላት ።
ደመወዝ
• በስምምነት
ጾታ
• ሴት
ብዛት
• ሁለት(2)
የስራ ቀንና ሰዓት
• ከሰኞ እስከ እሁድ ሆኖ በሳምንት አንድ ቀን እረፍት ይሰጣል።
• የስራ ሰዓት በሽፍት ሆኖ የጠዋት ሲሆኑ ከንጋት 12፡00 እስከ ቀን 9፡00 ሰዓት የከሰዓት ሽፍት ሲሆኑ ከቀን 7፡00 እስከ ምሽት 3፡00 ሰዓት ነዉ።
ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
• በእንግዳ ተቀባይነት ፣ በካሸሪ ስራ የሰሩበት የስራ ልምድ ኮፒ፣
• የት/ት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ፣
• ፋይዳ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ፣
• ፈተናዉን ካለፈ በኋላ ዋስ/ተያዥ ማቅረብ የሚችል፣
አድርሻ
አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ ሮቤራ ካፌ አጠገብ
በጅም ቤት ዉስጥ በሪሰፕሽኒስት & በካሸሪነት ከ2 ዓመት በላይ የስራ ልምድ ያላትና ለጃክሮስ ቅርብ የሆነች አመልካች ብቻ ለበለጠ መረጃ 0910662428 መደወል ይቻላል፣