Outdoor Sales Officer (የውጭ ሽያጭ ሠራተኛ)
Not specified
ስለ ሥራው
ድርጅቱ በተለያዩ አካባቢዎች የውጭ ሽያጭ ሥራዎችን የሚያከናውኑ 20 የሽያጭ ሠራተኞችን (Outdoor Sales Officer) አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- በተመደቡባቸው አካባቢዎች በመንቀሳቀስ አዳዲስ ደንበኞችን መፈለግና መመዝገብ
- የድርጅቱን አገልግሎት ማስተዋወቅና ለደንበኞች ግልጽ በሆነ ሁኔታ ማብራሪያ መስጠት
- የድርጅቱን የስራ መመሪያ ማክበር
- ከደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ማበረታታት
- ከደንበኞች ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን እና ፈጣን ምላሽ መስጠት
- በተመደቡባቸው የኮንዶሚኒየም እና ሌሎች አካባቢዎች የውጭ ሽያጭ ሥራዎችን ማከናወን
- የዕለት የሽያጭ እና የደንበኞች ምዝገባ ሪፖርት ማቅረብ
- የተመደቡ የሽያጭ ግቦችን በተከታታይ ለማሳካት መሥራት
መስፈርቶች
- 12ኛ ክፍል እና ከዛ በላይ ያጠናቀቀ/ቀች
- ከ 0 እስከ 1 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ
- የመኖሪያ አካባቢያቸው አያት፣ ሰሚት፣ ኮዪፊቼ፣ አራብሳ እና አድዋ ኮንደሚንየም ለሆኑ አመልካቾች ቅድሚያ ይሰጣል
ጥቅማ ጥቅሞች
- ደመወዝ 6,000.00 ብር
- ዕለታዊውን የምዝገባ ግብ ላሳኩ ተጨማሪ የኮሚሽን ክፍያ
- በ 2 ወር የሙከራ ጊዜ ጥሩ የሥራ ውጤት ላሳዩ ውል የማራዘም እና ወደ Sales Representative የማደግ ዕድል
እንዴት ማመልከት ይቻላል
አመልካቾች ሲቪያቸውን እና የሚገኙበትን ስልክ ቁጥር በመጥቀስ አመልክት/ቺ የሚለውን በመጫን ማመልከት ይችላሉ። የማመልከቻ ማብቂያ ቀን November 9, 2026።