የፋሽን ዲዛይነር (Fashion Designer)
Private Client
ስለ ሥራው
ድርጅቱ አዳዲስ እና ማራኪ የሆኑ የልብስ ዲዛይኖችን የሚያዘጋጅ ባለሙያ የፋሽን ዲዛይነር በሙሉ ጊዜ ቅጥር ይፈልጋል።
ኃላፊነቶች
- አዳዲስ እና ማራኪ የሆኑ የልብስ ዲዛይኖችን በዕጅ ወይም በዲጂታል ፕሮግራሞች ማዘጋጀት
- ለምርት የሚሆኑ ንድፎችን እና የናሙና (Prototype) ሥራዎችን መስራት
- ለዲዛይኖቹ የሚሆኑ ጥራታቸውን የጠበቁ ጨርቆችንና ማሰሪያ እቃዎችን መምረጥና ማሰባሰብ
- የገበያውን የፋሽን አዝማሚያዎች ማጥናት እና ከዘመኑ ጋር የሚጣጣሙ ስብስቦችን ማቅረብ
- ከስፌት እና ከምርት ቡድን ጋር በቅርበት በመስራት የዲዛይኑ ጥራትና ትክክለኛነት መጠበቁን ማረጋገጥ
መስፈርቶች
- በፋሽን ዲዛይን ወይም ተዛማጅ መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's Degree) ወይም ተስማሚ የሙያ ማሰልጠኛ (TVET) ምስክር ወረቀት
- በፋሽን ዲዛይነርነት ወይም ተዛማጅ ሥራ ላይ ከ2-3 ዓመት የሥራ ልምድ
- የናሙና አሰራር (Pattern making) እና የስፌት ክህሎት ያለው (ተመራጭ)
- ከፍተኛ የፈጠራ (Creativity) እና የውበት ስሜት
- ስለ ጨርቅና ከለር ምርጫ ጥሩ እውቀት
- በቡድን የመስራት እና ጥሩ የመግባባት ችሎታ
እንዴት ማመልከት ይቻላል
በሚከተለው ስልክ ቁጥር ያመልክቱ፡ 0994872344