P
ፋርማሲስት ወይም ድረጊስት
Private Client
ስለ ሥራው
መድኃኒት ቤታችን ታታሪ፣ ስራውን አክባሪ እና በማኅበራዊ ሚዲያ (ለምሳሌ TikTok) ማስታወቂያ ለመስራት ፍላጎት ያለው ጀማሪ ፋርማሲስት ወይም ድረጊስት በጉርድ ሾላ፣ አዲስ አበባ መቅጠር ይፈልጋል።
ዋና ዋና የሥራ ኃላፊነቶች
- መድኃኒቶችን በትክክልና በሙያዊ ሥነ-ምግባር መሠረት ለደንበኞች ማቅረብ
- ስለ መድኃኒቶች አጠቃቀም እና ጥንቃቄዎች ተገቢውን ሙያዊ ምክር መስጠት
- በTikTok እና በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚቀርቡ የጤና ትምህርትና የመድኃኒት ቤቱ ማስተዋወቂያዎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ
- ለደንበኞች ጥሩ አገልግሎት መስጠት እና ከሥራ ባልደረቦች ጋር በትብብር መሥራት
የሚፈለጉ ብቃቶች
- በፋርማሲ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ (1 ዓመት የሥራ ልምድ) ወይም ዲፕሎማ (3 ዓመት የሥራ ልምድ)
- ጥሩ የተግባቦት ችሎታ እና የደንበኛ አገልግሎት ክህሎት
- በTikTok እና በሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይዘት (content) ለመፍጠር እና በቪዲዮ ለማቅረብ ፍላጎትና ተነሳሽነት
እንዴት ማመልከት ይቻላል
ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የሥራ ልምዳችሁን የሚገልጽ CV እና የትምህርት ማስረጃችሁን መላክ ትችላላችሁ።